top of page

የጉብራቅ (ግቭር-አቑ ) ተራራ

  • Writer: Wag Ethiopia
    Wag Ethiopia
  • Nov 25, 2022
  • 2 min read

መገኛ/Location

ጉብራቅ (በአገውኛ ግቭር-አቑ) ተራራ በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ፤ በጋዝጊብላ ወረዳ፤ በ018 ዛሮታ ቀበሌ፤ በጉብራቅ ጎጥ ይገኛል።



ተፈጥሮ/Landscape

ተራራው ተፈጥሮአዊ አቀማመጡን ስንመለከትም ጥርብ ከመሰለ የአለት የተፈጥሮ ድንጋይ የተገኘና ዙርያውም በሰው ልጅ እጅ-ጥበብ የተጠረቡ የሚመስሉ ገደላ ገደሎች ያለውና አይን ማራኪ፤ ለመንፈስ ርካታን የሚፈጥር ነው። ተራራው በአረንጓዴ ተክሎች የተከበበና ዙርያው ረግረጋማ የሆነና የአካባቢው ነዋሪዎች ክረምት እስከ በጋ ለምድ ለብሰው የሚንቀሳቀሱበት የአየር ንብረት ያለዉ ነዉ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በስሩ ያለው ደን እየተመነጠረ የውሃ ምንጮች እና ረግረጋማ ቦታዎች እየደረቁ በመሆናቸው ሳቢና ማራኪነቱ እንዲቀንስ አድርጎታል። ወደ ተራራው ለመውጣት ልምድ ያላቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ካልሆኑ በስተቀር በጣም አስቸጋሪ ውጣ ውረድን ማለፍ ይጠበቅብናል። በተራራው ጫፍ ላይ ከወጣን ቡኋላ ከከፍታዉ የተነሳ በአራቱም አቅጣጫ ያሉ አካባቢዎችን ለማየት የሚያስችል ነው። ወደ ተራራው ስንወጣ ያየነውን የመንፈስ ቁርጠኝነት ስንወርድም የሚያጋጥም በመሆኑ ምራቅን ዋጥ ማድረግ ያስፈልጋል።


የሰው አሻራ/Human Footprint

ሌላው አስገራሚው ነገር በተራራው ላይ ያሉት ከንጹህ አለት ተፍልፍለዉ የተዘጋጁት ባህላዊ የገበጣ መጫዎቻ፣ ጉድጓዶች ፣ የሙቃጫና ገበታ ቅርጽ ያላቸዉ ጉድጓዶች ይገኙበታል። ጉብራቅ በአገውኛ ግቭር-አቑ (የገበታ ውሃ) ከሚለው ቃል የተገኘ ነው። እነዚህ ጉድጓዶች “እንዴትና በማን ተሰሩ?” ብለን ያነጋገርናቸዉ የአከባቢው ታላላቅ ሰዎችም “በጥንት ጊዜ የአካባቢዉ ነዋሪዎች ጠላት ሲመጣባቸዉ አስቸጋሪዉን የተራራዉ ገደል ወጥተዉ እቃቸዉን በዛ በተራራዉ ያስቀምጡ እንደነበረና ኑሯቸዉንም በዛ ይገፉ እንደነበረና በዚህ ወቅት እነዚህን ገበጣዎች ለመጫወት የገበታዉንና የሙቀጫዉን ጉድጋድ ለዕለት ተለት ስራቸዉ መጠቀሚያነት ከዐለት” እንደሰሯቸዉ ይነገራል። እነዚህ የጥበብ ስራዎችም ከማይጠበቅ ዐለት ላይ ተጠርበዉ ለሚያያቸዉ ሰዉ “እንዴት?” የሚል ጥያቄን በህሊና ያጭራሉ። በሌላ በኩል በጊዜዉ የነበሩትን ሰዎች የጥበብ ምጥቀትም ያመላክታል።






ብዝሐ ሕይወት/Biodiversity

በተራራው ላይ 0.25 ሄክታር የሚሆን ሜዳማ ቦታ የሚገኝ ሲሆን በውስጡ እንደ አስት፣ ጭማ ሳር፣ ሙጃ፣ ኮይሎ የመሳሰሉትን እጸዋቶችና እንደ ሚዳቆ፣ ጦጣ፣ ሰሳ የመሳሰሉት እንስሳት የሚገኙበት ሲሆን እነዚህን ውብና ለመንፈስ እርካታ የሚሰጡ የመሰህብ ሃብቶችን ያቀፈ ነው።



ቱሪዝም/Tourism

በአሁኑ ስአትም ያለው የአየር ሁኔታ የውሃ አቅምና የተፈጥሮ አቀማመጥ ለኑሮ አመች በመሆኑ አካባቢው ያለበትን የመልማት፣ የደን ጭፍጨፋ፣ ህገ ወጥ አደን በመከላከል ለወደ ፊቱ የቱሪስት መስህብ በማድረግ የህዝቡ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የበኩላቸንን ድርሻ መወጣት ይጠበቅብናል። ቅርሶችን በመጠበቅና በመንከባከብ ለጥቅም ልናውላቸው ይገባል። እርስዎም ከወዳጅ ዘመድዎ ጋር የጉብራቅ (ግቭር፡አቑ ) ተራራን ይጎብኙ፣ ይስተዋውቁም።




[ምንጭ: የዋግ ኽምራ የጋዝጊብላ ወረዳ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የFacebook ገጽ ህዳር 15/2015 ዓ.ም]



 
 
 

Comments


Contact Us

Phone:+251-115 549493, Addis Ababa

Phone: +251-334 400424, Sekota

Connect with us
SUBSCRIBE

Thanks for submitting!

WDA is a local CSO registered in Ethiopia (Reg. No. 1855)

© 2023 Wag Technical Advisory Council (WTAC). Proudly created with Wix.com

bottom of page